Skip to main content
Loading...

ሀገሬ ፣ ኢትዮጵያ የፍቅሬ ኪዳኔ

ኢትዮጵያ የፍቅሬ ኪዳኔ ትዳሬ ነይ ፍቅር እንውለድ  ነይ ፍቅር እንዝራ  ነይ ትውልድ እንውለድ ነይ ፍቅር እናፍራ  ጊዜን የቀደመ  ጊዜን የሚመራ ህሊናው የነቃ  ምግባሩ የጠራ አሸናፊ ትውልድ ፊት አውራሪ አውራ ምርጥ ዘር ይብዛልሽ   እንደ እንቁ የሚያበራ  በልጆሽ ብርታት  ይሙላብሽ የደስ ደስ ቁንጅናሽ ይመለስ ውበትሽ ይታደስ ስምሽ በአለም ዙሪያ ይመስገን ይወደስ ፍሬሽ ለዓለም ይሁን  ይባረክ ይቀደስ

ኢትዮጵያ ሀገሬ ትዳሬ  ቃልኪዳኔ ፍቅሬ ታላቅ ሁኝ ክበጂ ሀያል ሁኝ ፍረጂ አሜን እልልታሽ ከፍ ይበል ድልሽን አውጂ አሜን ሀገሬ  ትዳሬ ሀገሬ-ትዳሬ በልጆሽ ጥበብ ተዋቢ አጊጪ አሜን ከሰማይሽ በላይ ከራስሽ ብለጪ አሜን

ሀገሬ  ትዳሬ ሀገሬ ትዳሬ  ኢትዮጵያ የፍቅሬ ኪዳኔ ትዳሬ ነይ ፍቅር እንውለድ  ነይ ፍቅር እንዝራ ነይ ትውልድ እንውለድ  ነይ ፍቅር እናፍራ ዘመንን እንርታ ጊዜን አንብለጠው ልኩን እናሳየው በፍኝ እንጠብጠው በብርሃን ተጉዘን ጊዜን እንለፈው ዘመንን ተርጉመን በመልካም እንፃፈው

በልጆሽ ብርታት ይሙላብሽ የደስ ደስ ቁንጅናሽ ይመለስ  ውበትሽ ይታደስ ስምሽ በአለም ዙሪያ- ይመስገን ይወደስ ፍሬሽ ለአለም ይሁን  ይባረክ ይቀደስ ኢትዮጵያ  የፍቅሬ ኪዳኔ ትዳሬ ታላቅ ሁኝ ክበጂ  ሀያል ሁኝ ፍረጂ አሜን እልልታሽ ከፍ ይበል ድልሽን አውጂ አሜን ሀገሬ ትዳሬ ሀገሬ ትዳሬ 
በልጆሽ ጥበብ ተዋቢ አጊጪ አሜን ከሰማይሽ በላይ ከራስሽ ብለጪ አሜን 
 

 

የይፋዊ  ሙዚቃ በሚካያ በሀይሉ

የሚካያ በሀይሉን የይፋዊ ሙዚቃ በYouTube ላይ እዚህ ያግኙ

👁 41 views
Mikaya Behailu
አርቲስት ሚካያ በሃይሉ
👁 41 views